Stay informed with our latest foundation updates, project progress, and community news.
በሀገራችን ከሚከበሩት ከፍተኛ የህዝብ አደባባይ በዓሎች መካከል የጥምቀት ሀይማኖታዊ በዓል በመላው ኢትዮጵያ በደማቅ ሁኔታ እንደሚከበር ይታወቃል፡፡በተለይ በጎንደር ደግሞ በየአመቱ እጅግ ደማቅ በመሆኑ ብዙ የውጭ ዜጎች,ዲያስፖራዎች እና ከተለያዩ የአለም ሀገራት እንዲሁም በሀገር ውስጥ በጎንደር ጥምቀትን ለማክበር በየዓመቱ ይገኛሉ፡፡ይህንን ምክንያት በማድረግ በጥምቀት ወቅት በጎንደር፣ በትክል ድንጋይ እና በግንድ መጣያ አካባቢዎች ድርጅቱን የማስተዋወቅ ስራ ለመስራት የተለያዩ ተግባራት ተከናውኗል፡፡